book Created with Sketch.

Group Created with Sketch.

data_cloud Created with Sketch.

orb Created with Sketch.

Created by potrace 1.14, written by Peter Selinger 2001-2017

mobile_key Created with Sketch.

what_to_do.svg Created with Sketch.

list Created with Sketch.

ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ሰዎችና የንግድ ድርጅቶች ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር የግል  የሆኑ ብዙ መረጃዎች በኢንተርኔት ወይም በድህረ ገፆች ላይ ይከማቻሉ ከዚያም ይላካሉ። በስልክዎ ላይ ወይም በታብሌትዎና በኮምፒውተርዎ ወስጥ ስለሚያስቀምጡት መረጃ ወይም በኢንተርኔት ካፌዎች ስለሚያገኙት መረጃ ያስቡ። ኢሜይልዎ፣ ፎቶዎን፣ መልእክትዎን፣ የባንክ መረጃዎን፣ የስራ፣ የመዘገቡትን የአድራሻዎች ዝርዝር እና ሌሎችም። እነዚህ መረጃዎች እንዲጠፉ ወይም በሌላ ሰው እጅ እንዲገቡ አይፈልጉም። እርስዎም ሆኑ ጓደኞችዎና ቤተሰቦችዎ የኢንተርኔት ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ጥሩ የሆነ “ዲጂታል ንፅህናን” እንደሚጠብቁ ያረጋግጡ።

ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ጤናማ የሆነ አጠቃቀም እንዲኖርዎት እነዚህን ፈጣንና አጫጭር ነጥቦች ጥቅም ላይ ማዋል ይጀምሩ። በበለጠ ደግሞ ከስር የተዘረዘሩትን ጠቃሚ ምክሮች “ፕሮ ቲፕስ” ይጠቀሙ።

wifi Created with Sketch.

የጋር ኮምፒውተሮች፣ ኢንተርኔት ካፌዎችና ለሁሉም ክፍት የሆነ ዋይፋይ

ከመሄድዎ በፊት ከኢሜይልዎ ይውጡ ወይም ሎግ አውት ያድርጉ
ከመሄድዎ በፊት ከማህበራዊ ሚዲያ መለያዎችዎ ይውጡ ወይም ሎግ አውት ያድርጉ
ጠቃሚ ምክር፡ የሚጎበኙትን ድረ ገጽ ደህንነቱ አስተማማኝ እንዲሆን ለማድረግ ቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትዎርክ (Virtual Private Network (VPN)) ይጠቀሙ
ከመሄድዎ በፊት ከኮምፒውተርዎ ይውጡ ወይም ሎግ አውት ያድርጉ፣ በተለይ በኮምፒውተር ካፌዎች ውስጥ
ከመሄድዎ በፊት የተመለከቷቸውን ገጾች ታሪክ ያጽዱ

password Created with Sketch.

የይለፍ ቃሎች

የይለፍ ቃልዎን ለሌላ ሰው አይንገሩ
በማህበራዊ ሚዲያና ኢሜይል መለያዎችዎን ባለ 2-ደረጃ ማረጋገጫዎችን ይጠቀሙ
ጠንካራ የሆነና የሚያስታውሱት የይለፍ ቃል ወይም ሃረግ ይፍጠሩ
የይለፍ ሃረግ ለመፍጠር ይሞክሩ፡ ለእያንዳንዱ መለያዎ የሚያስታውሱት አረፍተ ነገር ያስቡ
ለሚጠቀሙት ለእያንዳንዱ መለያ የተለያየ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ
ጠቃሚ ምክር፡ የይለፍ ቃሎችዎን ለመቆጣጠር እንዲያመችዎ የይለፍ ቃል ማስቀመጫ ወይም የይለፍ ቃል ማስተዳደሪያ ይጠቀሙ
የይለፍ ቃልዎን ለማንም አያሳውቁ

accounts Created with Sketch.

መለያዎች፡ ኢሜይል እና ማህበራዊ ሚዲያ

ጠቃ ምክር፡ በ HTTP ሳይሆን በ HTTPS የሚጀምሩ ድረ ገጾች ላይ ብቻ በመለያ ይግቡ
ያልተጠበቁ ኢሜይሎችና አባሪዎች ሲደርስዎት ይጠንቀቁ (ቫይረሶች ሊሆኑ ይችላሉ)
የሚከፍቷቸው አገናኞችና የሚያወርዷቸው ፋይሎች ከሚያውቋቸው ሰዎች የተላኩ ብቻ ይሁኑ
ያልተጠበቁ ወይም አጠራጣሪ ኢሜይሎች ሲደርስዎ ጓደኞችዎ ወይም የቤተሰብዎ አባል በእርግጥም ኢሜይሉን ልከውልዎ እንደሆነ ያጣሩ
በትክክል ያልተጻፉ ድረ ገጾች ላይ ያሉ አገናኞችን አይንኩ

laptop Created with Sketch.

የግል መሳሪያዎች ደህንነት፡ ሞባይል ስልኮችና ላፕቶፖች

በስልክዎ እና በኮምፒውተርዎ ላይ ነጻ የቫይረስ መቆጣጠሪያ ይጫኑ
ኮምፒውተርዎ እና ስልክዎ ሃኪንግን ይበልጥ መቋቋም እንዲችሉ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማዘመኛዎችን ያውርዱ
ጠቃሚ ምክር፡ ስልክዎን እና ኮምፒውተርዎን ኢንክሪፕት ያድርጉ
በስልክዎ እና በኮምፒተርዎ ላይ የይለፍ ቃል ወይም የይለፍ ኮድ ይጠቀሙ